ዜና
ቤተክርስቲያን

ACE HQ Front

የ2012 ዓ.ምን የአገልግሎት ጊዜያት ከእግዚአብሔር ከተቀበልን እነሆ ስድስት ወራቶችን አጠናቅቀን ሰባተኛውን ጀምረን እንገኛለን። በነዚህ የአገልግሎት ጊዜያቶች ውስጥ ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር ኃይልና እገዛ በርካታ ተግባራትን ያከናወነች ሲሆን፣ ከመስከረም 6/2012 ጀምሮ በተዘጋጀው መርሃግብር መሠረት በአዳማ፣ በሐዋሳ፣ በዲላ፣ በባህርዳር፣ በቦሬ፣ በደቡብ ኦሞ (ጂንካ)፣ በይርጋለም፣ በአለታወንዶ፣ በኦዶላ፣ በአርባምንጭ ፣ በሾኔ፣ በወላይታ ሶዶ፣ በአረካ፣ በነቀምቴ፣ በጅማ፣ በሆሳዕናና በአዲስ አበባ ቁጥራቸው ከ4000 በላይ ለሆኑ ለቤተክርሰቲያን ተተኪ ወጣቶች ሰፊ ስልጠና ተሰጥቶአል።

ከዚሁ ስልጠና በተጓዳኝ በነዚሁ ጊዜያት በሊበን(ሃረቀሎ)፣ በደሴ፣ በመቀሌ፣ በምዕራብ ወላይታ (በበሌ) የየሰበካዎቹ ዓመታዊ ጉባኤዎች የተካሄዱ ሲሆን ብዙ ሰዎች ለኃጢአታቸው ስርየት በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠምቀዋል፣ ጥቂት የማይባሉ ሰዎች በመንፈስ ቅዱስተሞልተው ለዳግም ልደት በቅተዋል።

ቤተክርስቲያን ወንጌልን በዓለም ሁሉ ለማዳረስ እግዚአብሔር ከሰጣት ተልዕኮ አንጻር ከኢትዮጵያ ውጪ በአውሮፓ ፣ በህንድ፣ በሱዳን፣ ደቡብ አፍሪካ…የየሐገራቱን አብያተክርስቲያናት ኣመታዊ ጉባኤዎች አካሄዳለች። በነዚህ ጉባኤዎች ቢሾፕ ደጉ ከበደ የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ዋና አስተዳዳሪ ተገኝተው የእግዚአብሔርን ቃል በማካፈል ለበረከት ሆነዋል።

Scroll to Top