በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ውጪ ላላችሁ ቅዱሳን በሙሉ

እጅግ የምንወዳቸውና የተከበሩ የእግዚአብሔር ሰው አባታችን ቢሾፕ ተክለማሪያም ገዛኸኝ ሰኔ 14 ቀን 2014 ዓ.ም ከዚህ አለም ድካም አርፈው ወደ አምላካቸው መሰብሰባቸው የሚታወቅ ነው::

ከዚህ በፊት በተለያዩ መንገዶች እንደተገለጸው የሽኝት ፕሮግራሙ በአዲስ አበባ ጎፋ ዋናው ጸሎት ቤት የተለያዩ የሃገር ውስጥ እና የውጪ ሃገራት እንግዶች በተገኙበት ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ ይካሄዳል::

ፍቅሩን ለመግለጥ የሚፈልገው የህዝብ ቁጥር በርካታ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ የሽኝት ፕሮግራሙ በዕለቱ ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅበት እስከ 8:30 ድረስ በደቡብ ቲቪ በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል::

በመሆኑም በሃገር ውስጥ እና በተለያዩ የአለማችን ክፍል የምትገኙ ቅዱሳን የእግዚአብሔር ልጆች በተጠቀሰው ቀን ዝግጅቱን በቀጥታ መከታተል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን::

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን!

Scroll to Top