የተተኪ ወጣቶች ስልጠና

“ቀጣዩ የእግዚአብሔር መንግሥት አገልግሎት በቀጣይ ትውልድ” በሚል ርዕስ ከሐገረ ስብከቱ የተለያዩ ሰበካዎችና ንዑስ ሰበካዎች የተውጣጡ ተተኪ አገልጋዮች ከነሐሴ 14-16 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዋናው ፀሎት ቤት ስልጠና ተካፍለዋል። በዚህ ስልጠና ላይ ቢሾፕ ደጉ ከበደ፣ ቢሾፕ ኢሳያስ አሻ፣ ቢሾፕ ጌታሁን ላምቤቦ በአሰልጣኝነት ትምህርት ያቀረቡ ሲሆን የአገልግሎት ኃላፊነትና መሰጠትየማያቋርጥ እድገትዶክትሪንና አያያዙየፀሎት ሕይወትና ድምፁን መስማት መለማመድየአመራርን ፀጋና ጥበብ ማሳደግበአገልግሎት ጅማሬ ላይ ያሉ ተግዳሮቶችን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ማለፍየግልና የአካል አገልግሎትየመጨረሻውን ዘመን የቤተክርስቲያን ክብር ማወቅዘላለማዊ ዋጋና ክብር ላይ ማተኮር በሚሉ አብይ ርዕሶች ላይ ያተኮሩ ሰፊ የስልጠና ማዕቀፎችን በመዳሰስ አሰልጥነዋል። ስልጠናው የበረከት የመነቃቃትና ራስን በአግባቡ ማየት ያስቻለም እንደነበር ከስልጠናው ተካፋዮች ማረጋገጥ ተችሏል።

የአገልጋዮች ሴሚናር

በኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ስር በሚገኙ የተለያዩ ሰበካዎችና ቅርንጫፍ ሰበካዎች በ30 ማእከላት መጨረሻውን ዘመን በመዋጀትወንጌልን ወዳልዳኑት በማድረስና ቤተክርስቲያንን ለመነጠቅ በማዘጋጀት ላይ ትኩረት አድርጎ ለወንጌል አገልጋዮች ከመስከረም-ህዳር 2014 ዓ.ም ሴሚናር ተስጥቶአል። በስልጠናውም የእግዚአብሔር ጉብኝት እና ለእግዚአብሔር ስራ መነቃቃት የነበረ ሲሆን ፕሮግራሙ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል። 

ሃዲያ ቅ/ሰበካ

ከከምባታና ሃዲያ ሰበካ የአገልጋዮች ሴሚናር በመቀጠል ከመስከረም 14-17/2014 ዓ.ም የሆሳዕና ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ኮንፍረንስ በሰሜን ሆሳዕና አጥቢያ ተካሂዶአል። በኮንፍራንሱ ጠቅላላ ምእመናን ከመታነጻቸው ባሻገር 130 ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ሲሞሉ 48 አዳዲስ ነፍሳት ለኃጢአታቸው ስርየት በጌታ በኢየሱስ ስም ተጠምቀዋል። በኮንፍራንሱም ቢሾፕ ጌታሁን ላምቤቦ፣ ቢሾፕ አለማሁ ገ/ሚካኤል፣ ቢሾፕ ተረፈ ፈካ እና ወንጌላዊ ቴዎድሮስ አልታዬ ተገኝተው ለበረከት ሆነዋል። ይኸው መንፈሳዊ እንቅስቃሴ በመቀጠል በመስከረምና በጥቅምት ወር ብቻ በቅ/ ሰበካው 595 ሰዎች ለኃጢአታቸው ስርየት በጌታ በኢየሱስ ስም ተጠምቀዋል።

አዲስ አበባ ቅ/ሰበካ 

በአዲስ አበባ ሰበካ የቀራንዮ አንፆኪያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን የፀሎት ቤት ምረቃ ጥቅምት 20 ቀን 2014 ዓ.ም ተካሂዷል። መጠኑ 9 በ 16 በሆነው በዚህ የፀሎት ቤት ምረቃ ላይ የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ዋና አስተዳዳሪ ቢሾፕ ደጉ ከበደ፣ የአዲስ አበባ ሰበካ ኃላፊ ቢሾፕ ተረፈ ፈካ፣ የአዲስ አበባ የንዑስ ሰበካ ሃላፊዎችን መጋቢዎች፣ ቢሾፕ በቀለ ፈዬ፣ እህት ሜሪ ጎስታላ፣ እህት ምዕራፍ ዕቁባይ፣ እህት አለምነሽ አበራ ተገኝተዋል።

በአዲስ አበባ ሰበካ የለቡ-ኢየሩሳሌም ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን የፀሎት ቤት ምረቃ ህዳር 11 ቀን 2014 ዓ.ም ተካሂዷል። መጠኑ 9 በ 24 በሆነው በዚህ የፀሎት ቤት ምረቃ ላይ የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ዋና አስተዳዳሪ ቢሾፕ ደጉ ከበደ፣ የአዲስ አበባ ሰበካ ኃላፊ ቢሾፕ ተረፈ ፈካ፣ የአዲስ አበባ የንዑስ ሰበካ ሃላፊዎች፣ መጋቢዎችና ሌሎች ቅዱሳን ተገኝተዋል።

ኬንያ

ለምስራቅ አፍሪካ አገልጋዮች ከመስከረም 26-30 ቀን 2014 ዓ.ም በኬንያ ናይሮቢ በአለም አቀፍ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ቼር ማን ቢሾፕ ደጉ ከበደ ሴሚናር ተስጥቶአል። በሴሚናሩም በጉባኤው ከ30 በላይ የሚሆኑ ኬንያውያን የወንጌል አገልጋዮች የተሳተፉ ሲሆን ሴሚናሩ በታላቅ በረከት ተጠናቋል። ከሴሚናሩ በኋላ የአንድ ቀን ኮንፍራንስ የነበረ ሲሆን 23 ሰዎች ለሃጢአታቸው ስርየት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠምቀዋል፣ 15 ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተዋል።

አንጎላ

ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ ከኢትዮጵያ ለስራ በሄዱ ወንድሞችና እህቶች በተተከለችው የአንጎላ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ከጥቅምት 24-28 ቀን 2014 ዓ.ም ኮንፍራንስ የተደረገ ሲሆን የአለም አቀፍ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ቼር ማን ቢሾፕ ደጉ ከበደ በመገኘት ለቤተክርስትያኒቱ አገልጋዮች ሴሚናር ሰጥተዋል። በነበረውም ኮንፍራንስ 28 አንጎላውያን ለሃጢአታቸው ስርየት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠምቀዋል፣ ለአምስት የወንጌል አገልጋዮችም የስብከትና የክህነት ፈቃድ ተሰጥቶ ጉባኤው በታላቅ ድልና በረከት ተጠናቋል።

Scroll to Top