በአገር ውስጥና በውጭ አገራት ለምትገኙ የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ምዕመናንና አገልጋዮች የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋሰላምና በረከት ይብዛላችሁ፡፡ ከእግዚአብሔር ቃል የምናስተላልፈው ይህ መልዕክት በያላችሁበት ይድረሳችሁእናንተ ደግሞ ለሌሎች አስተላልፉት፡፡

  የእኛ አኗኗርና አካሄድ ስለ እኛ እንደተጻፈው ይሁን  

ወንድሞችና እህቶች፡- በእግዚአብሔር ቃል ስለ እኛ የተጻፈው የእኛን ማንነትከእኛ የሚጠበቀውን አካሄድና አኗኗር ከሌሎች የተለየ ያደርጋል፡፡ ሌሎች ልዩ ልዩ ወቅታዊ ሁኔታዎችንና የመጨረሻውን ዘመን የሚያስተናግዱባቸው የየራሳቸው አካሄድ አላቸው፡፡ እኛ ግን ሁኔታዎችንና ዘመኑን ማስተናገድ ያለብን በመጽሐፍ ቅዱስ ስለ እኛ ማንነትስለሚጠበቅብን አኗኗርና አካሄድ እንደተጻፈው ነው፡፡ ገላ. 3፡26-29 ላይ ስለ እኛ ማንነት የተጻፈው በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁናከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና፡፡ አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለምባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለምወንድም ሴትም የለምሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና፡፡ እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ፡፡” ይላል፡፡ በ2ኛ.ቆሮ.5፡17 ላይ ያለው ቃል-“ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነውአሮጌው ነገር አልፎአልእነሆ ሁሉም አዲስ ሆኖአልይላል፡፡  

በዚህ መሠረት የእኛ የቀድሞ ማንነታችን ተለውጦልዩነቶቻችንም ተወግደውበክርስቶስ አዲስ ሰውና በአንድ አካል ያለን ብልቶች ተደርገናል፡፡ ስለዚህ እኛ መመላለስ የሚገባን ስለ እኛ እንደተጻፈው ነው፡፡ 

በ1ኛ.ጴጥ.1÷23 ላይ የተጻፈው እኛን ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም÷ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ፡፡” ይለናል፡፡ እንዲሁም1ኛ.ጴጥ.2÷9-10 ላይ እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትነግሩ የተመረጠ ትውልድ÷ የንጉሥ ካህናት÷ ቅዱስ ህዝብ÷ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁእናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁእናንተ ምህረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም አሁን ግን ምህረትን አግኝታችኋል፡”ይለናል፡፡   

ስለዚህ ከእኛ የሚጠበቀው እንደ ተመረጠ ትውልድእንደ ንጉሥ ካህናትእንደ ቅዱስ ሕዝብእንደ እግዚአብሔር ወገን ስለ እኛ እንደተጻፈው አካሄድ መኖር ነው፡፡ 

 የምንኖርበት ዓለም በልዩ ልዩ ነባርና አዳዲስ ክስተቶች የተሞላ ነው፡፡ አሁን ያለንበትና የሚመጣው ዘመን በእግዚአብሔር ቃል ስለዘመኑ የተጻፈው ሁሉ በየተራው የሚፈጸምበት ነው፡፡ በእነዚያ ክስተቶችና በዘመኑ ሁኔታዎች መካከል እኛ መኖርና መመላለስ የሚገባን እንደ ሌሎች እና እንደ ሁኔታዎቹ እየተለዋወጥን ሳይሆን ስለ እኛ እንደተጻፈው ነው፡፡

ማቴ.5÷13-16 የተጻፈው እናንተ የምድር ጨው ናችሁእናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ….. መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ፡፡” ይለናል፡፡  

ስለዚህ አካሄዳችንአኗኗራችንና ተግባራችን የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ለሰዎች የሚገልጥ ሊሆን ይገባዋል፡፡  ፊል.2÷14-16 የተጻፈው በመጥፎና በጠማማ ትውልድ መካከል ያለ ነቀፋ የዋሆችም ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች እንድትሆኑ ሳታንጎራጉሩ ክፉም ሳታስቡ ሁሉን አድርጉበእነርሱም መካከል የሕይወትን ቃል እያቀረባችሁ በዓለም እንደ ብርሃን ትታያላችሁ….” ይለናል፡፡ ስለዚህ ከእኛ የሚጠበቀው ስለ እኛ እንደተጻፈው መኖር ነው፡፡ 

እኛ ኤፌ. 5÷8-10፤ ከቁጥር 15-17 እንደተጻፈው እንመላለስ፡፡ እግዚአብሔር ብርሃን ነውእኛ ደግሞ የብርሃን ልጆች ነን፡፡ እኛ ስለ እኛ እንደተጻፈው ለጌታችን ደስ የሚያሰኘውን እየመረመርን እንደ ብርሃን ልጅነታችን እንመላለስ፡፡ እንዲሁም እኛ ይህን የመጨረሻውን ዘመን እንዋጀው፡፡ እኛ ዘመኑን እንቆጣጠረው እንጂ ዘመኑ እኛን አይቆጣጠረን፡፡ እኛ ዘመኑን እንግዛው እንጂ ዘመኑና የዘመኑ ሁኔታዎች እኛን አይግዙን፡፡

ይህ የመጨረሻው ዘመን ሁለት ገጽታዎች ያሉት ነው፡፡ አንዱ የዘመኑ ገጽታ በኢሳ. 60÷1-3 እና በማቴ.24÷ 3-14 እንደተጻፈው ምድርን ድቅድቅ ጨለማ የሚሸፍንበትና ብዙ የሚያሰምጡ ክስተቶች የሚፈጸሙበት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የእግዚአብሔር መንግስት ወንጌል በዓለም ሁሉ የሚሰበክበት ነው

አንዱ መጥፎና ፈታኝ ገጽታ ሲሆን ሁለተኛው እጅግ በጣም ደስ የሚያሰኝ ብዙ የእግዚአብሔር ተስፋ ቃሎች የሚፈጸሙበት ገጽታ ነው፡፡ ስለዚህ እኛን የዘመኑ ክፉና ፈታኝ የሆነው ገጽታ ሊገዛን አይገባምይልቁንስ እኛ የእግዚአብሔርን ተስፋ ቃሎች ይዘን ለእኛ እንደሚገባን እየተመላለስን ዘመኑን መግዛት ይገባናል፡፡ እኛ ይህን የመጨረሻውን ዘመን መዋጀት የምንችለው ስለ እኛ እንደተጻፈው በመመላለስ መኖር ስንችል ነው፡፡ 

ዘመኑ ከእንቅልፍ የምንነሳበትና በአግባብ የምንመላለስበት ነው (ሮሜ 13÷11-14)፡

ዘመኑ መንቃት ያለብንና በመጠን መኖር ያለብን ነው (1ተሰ.5÷1-8)፡ 

ዘመኑ የጌታ ቀን ድንገተኛ እንዳይሆንብን የምንጠነቀቅበትና ሁልጊዜ በጸሎት መትጋት ያለብን ነው (ሉቃ.21÷34-36)፡

ዘመኑ የሚያስቱ መናፍስትና የአጋንንት ትምህርት የበዛበት በመሆኑ እኛ በመልካም ትምህርት መጋቢነት መትጋት ያለብን ነው (1ጢሞ.4÷1-6)፡ 

ዘመኑ እኛ እግዚአብሔርን ለመምሰል መትጋት ያለብን ነው (1ጢሞ.4÷7-10)፡ 

ዘመኑ ራሳችንንም የሚሰሙንንም ለማዳን ለራሳችንና ለትምህርታችን መጠንቀቅ ያለብን ነው (1ጢሞ. 4÷11-16)፡ 

ዘመኑ ለአስጨናቂነቱ ምክንያት ከሆኑት ክፉ ሰዎችና ከአካሄዳቸው መራቅ ያለብን ነው (2ጢሞ.3÷1-5)፡ 

ዘመኑንና ሁኔታዎችን በድል አድራጊነት ለመሻገር እኛ ስለ እኛ እንደተጻፈው እየተመላለስን እንኑር፡፡  ለሁኔታዎች በእግዚአብሔር ቃል መሠረት ተገቢውን ምላሽ እንስጥ፡፡ 

 • በመዳን ትምህርታችን እንጽና (2ጢሞ.3÷14-17)፡ 
 • የእግዚአብሔር ሰዎችን መልካም ምሳሌነት እንከተል (2ጢሞ.3÷10-12)፡ 
 • ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አንጠመድ (2ቆሮ.6÷14-18)፡ 
 • እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በልባችን መታደስ እንለወጥ እንጂ ይህን ዓለም አንምሰል (ሮሜ 12÷2)፡ 
 • ምን እንድንሰማ እንጠበቅለራሳችንም እንጠንቀቅ (ማር.4÷24፣ ሉቃ. 21÷25-36)፡ 
 • እኛ በክስተቶች አንፍራ÷ አንጨነቅይልቁንስ ሊመጣ ካለው ሁሉ ለማምለጥና በጌታችን በኢየሱስ ፊት ለመቆም እንድንችል ሁልጊዜ በጸሎት እንትጋ (ሉቃ.21÷25-26)፡ 

በማቴ.24÷12 የተጻፈው የመጨረሻው ዘመን የዓመፃ ብዛት ፍቅራችንን እንዳያቀዘቅዝብን እንጠንቀቅ፡፡ እኛ ስለ እኛ እንደተጻፈው እናድርግ፡፡ 

 • እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንት ሁሉ ሳንታክት እንጸልይ (1ጢሞ.2÷1-2)፡ 
 • በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣናት በአገባቡ እንገዛ (ሮሜ 13÷1-7)፡ 
 • ክፉውን ነገር እንጸየፈውከበጎ ነገር ጋር እንተባበር (ሮሜ 12÷9)፡ 
 • ቢቻለን ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም እንኑር (ሮሜ.12÷18)፡ 
 • ጊዜ ካገኘንና መልካም ማድረግ ሲቻለን ለሰው ሁሉ ይልቁንም ለሃይማኖት ቤተሰዎች መልካም እናድርግ (ምሳ.3÷27-28፣ ገላ.6÷10)፡ 
 • ድሆችን እናስብ (ገላ.2÷10)፡ 
 • ወላጆች የሌላቸውን ልጆችና ባልቴቶችን በመከራቸው እንጠይቅ (ያዕ.1÷27)፡ 
 • ለተራቡትና ለስደተኛ ድሆች ከእንጀራችን እንቁረስላቸው (ኢሳ. 58÷7)፡ 

ለወቅታዊ ችግሮች በጊዜያዊ መፍትሔነት የሚወሰዱት ጊዜያዊ እርምጃዎች ስለ እኛ የተጻፈውን እንዳያዘናጉን ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡

ሁኔታዎች ቀስ በቀስ ወደ ነበሩበት እስኪመለሱም ሆነ ሙሉ በሙሉ ሲስተካከሉ እኛም ስለ እኛ እንደተጻፈው ልንኖርና ልንመላለስ ይገባናል፡፡ 

 • ወቅታዊ ችግሮችን ለማለፍ ለሰዎችና ለመንግሥት ሥርዓት እንገዛ (1ጴጥ.2÷13-17)፡ 
 • ወቅታዊ ችግሮች ሲያልፉ ዕብ.10÷25፣ 1ቆሮ.16÷20 እንደተጻፈው በየአጥቢያዎቻችንበየኮንፈረንሶቻችንና በየሥራ ስብሰባዎቻችን መሰብሰብን አንተውበተቀደሰ አሳሳም እርስ በርሳችን ሰላምታ ወደ መሰጣጣትም እንመለስ፡፡ 

በልዩ ልዩ ክስተቶችበወቅታዊ ችግሮችና በዘመኑ ሁኔታዎች ሳንወሰን ሃይማኖታዊ ተግባራቶቻችንንና ተልዕኮአችን ሳንታክት እንፈጽም፡፡ 

 • በጊዜውም አለጊዜውም ቃሉን እንስበክነገርን ሁሉ በልክ እናድርግአገልግሎታችንን እንፈጽም (2ጢሞ.4÷1-5)፡ 
 • ከዕለታዊ ተግባሮቻችን ጋር ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም መምጣት ተዘጋጅተን እንኑር (ማቴ.24÷36-44)፡ 
 • በተጠራንበት መጠራታችን እንደሚገባ እንመላለስ (ኤፌ.4÷1-16)፡ 
 • ልባሞች ሆነንመብራታችንን እያበራንከመብራታችን ጋር በመቅረዛችን ዘይት ይዘንበተሰጠን ልዩ ልዩ መክሊት እየተጋን ነቅተንና ተዘጋጅተን እንኑር (ማቴ.25÷1-17)፡ 
 • ምሕረትን እንድንቀበልና በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ (ዕብ.4÷14-16)፡ 
 • መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክት (2ተሰ.3÷6-13)፡ 

ዘመኑን እየዋጀን÷ በውጭ ባሉት ዘንድ በጥበብ እንመላለስ (ቆላ.4÷5)፡ 

እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንደምንመላለስ በጥንቃቄ እንጠበቅ (ኤፌ.5÷15)፡ 

ጌታም በነገር ሁሉ ማስተዋልን ይስጠን፡፡ (2ጢሞ.2÷7) 

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ለሁላችንም ይብዛልን፡፡ አሜን!! 

Scroll to Top