የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን አመሰራረትና እድገት

ጸሃፊ፡-                            ቢሾፕ በቀለ ፈዬ

የታተመበት ቦታና ዓ.ም.፡-         2012 ዓ.ም.፣ አዲስ አበባ 

አሳታሚ፡-                        የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያንፖ.ሳ.ቁ. 4442፣ ስልክ 251-114-660086 

አታሚ፡-                          ፋልከን አታሚዎች                    የገጽ ብዛት፡-         329

  መጽሐፉ የቤተክርስቲያኒቱን በኢትዮጵያ ምድር ከጅማሬው አንስቶ የመጀመሪያወን 50 ዓመታት ጉዞ የሚያስቃኝ ሲሆን በሁለት ክፍሎች የተከፈለ ነው፡፡ የመጀመሪያው አጠር ያለ ክፍል ቀደምት የእምነት አባት የሆኑትና ከጅማሬው አንስቶ ለ 40 ዓመታት ያህል ዋና አስተዳዳሪ (ከ 1961 – 2000 ዓ.ም.) እና ከ 2000 – 2007 ደግሞ የዓለም አቀፉ አገልግሎት ቼርማን ሆነው ባገለገሉት በቢሾፕ ተ/ማርያም ገዛኸኝ ሕይወትና አገልግሎት ዙሪያ ያተኩራል፡፡ ይህ ክፍል 81 ገጾችን ብቻ የያዘ ሲሆን የመጽሐፉን 17% ያህል ብቻ ይሸፍናል፡፡ ሁለተኛውና ሰፊው ክፍል (የቀረው 83%) በኢትዮጵያ በአራቱም አቅጣጫዎች የሐዋርያት እምነት እንዴት እንደተጀመረና የታለፈባቸው ታላላቅ ስደቶችና መከራዎች እንዲሁም የቤተክርስቲያኒቱን መስፋፋት የሚተርክ ነው፡፡

መጽሐፉ በ 15 ክፍሎች ተከፋፍሎ የቀረበ ሲሆን 14ቱ ክፍሎች የሐዋርያት ወንጌል የገባባቸውን የኢትዮጵያ አካባቢዎች እንደ አገባቡ በመመደብ የቀረበባቸው ናቸው፡፡ ወንጌል የገባባቸውን እያንዳንዱን ቀበሌና ወረዳ ዘርዝሮ ማቅረብ የማይሞከር በመሆኑ በዚያ አካባቢ ወንጌል ቀድሞ የገባባቸውን ቦታዎችና ያጋጠሙ ስደቶችየተከፈሉ መስዋዕትነቶች እንዲሁም እግዚአብሔር የሰራቸውን ተዓምራት ጠቅለል ባለ መልኩ ብቻ ተካትተዋል፡፡ ይህም ተረካቢው የቤተክርስቲያን ትውልድ ጌታ ኢየሱስ የሰራቸውን ተዓምራትና የቤተክርስቲያንን ጉዞ ውጣ ውረዶች እንዲገነዘብና እርሱም መሰረቱን ሳይለቅ የአባቶቹን ተጋድሎ ተቀብሎ በመሰረቱ ላይ በማነጽ በትህትናና በጽድቅ እየተጓዘ የእነርሱን ፈለግ የሚከተል እንዲሆን እንደሚያግዘው ይታሰባል፡፡

Scroll to Top