“የደከሙትን እጆች አበርቱ፥ የላሉትንም ጕልበቶች አጽኑ። ፈሪ ልብ ላላቸው፦ እነሆ፥ አምላካችሁ በበቀል በእግዚአብሔርም ብድራት ይመጣልና፥ መጥቶም ያድናችኋልና በርቱ፥ አትፍሩ በሉአቸው። በዚያን ጊዜም የዕውሮች ዓይን ይገለጣል የደንቆሮችም ጆሮ ይከፈታል። በዚያን ጊዜ አንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘልላል፥ የድዳም ምላስ ይዘምራል፤ በምድረ በዳ ውኃ፥ በበረሀም ፈሳሽ ይፈልቃልና። ደረቂቱ ምድር ኵሬ፥ የጥማት መሬት የውኃ ምንጭ ትሆናለች፤ ቀበሮ የተኛበት መኖሪያ ልምላሜና ሸምበቆ ደንገልም ይሆንበታል።” [ኢሳይያስ 35፥3-7]
የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን 34ኛው ዋራ-ቤቴል አለምአቀፍ ጉባኤ በዋራ ሜዳ ላይ ከመጋቢት 5-7 ቀን 2017 ዓ.ም ይካሄዳል። እርስዎም የሁላችንንም ፈጣሪ የሆነው አንዱ አምላክ እግዚአብሔር ብቻ ወደሚመለክበትና የተለያዩ ሸክሞችን፣ ቀንበሮችንና በሽታዎችን ወደሚያራግፍበት መንፈሳዊ ጉባኤ መጥተው የበረከቱ ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ በኢየሱስ ፍቅር ተጋብዘዋል።
የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን
የካቲት 2017 ዓ.ም