“ቀጣዩ የእግዚአብሔር መንግሥት አገልግሎት በቀጣይ ትውልድ” በሚል ርዕስ ከሐገረ ስብከቱ የተለያዩ ሰበካዎችና ንዑስ ሰበካዎች የተውጣጡ ተተኪ አገልጋዮች ከነሐሴ 14-16 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዋናው ፀሎት ቤት ስልጠና ተካፍለዋል። በዚህ ስልጠና ላይ ቢሾፕ ደጉ ከበደ፣ ቢሾፕ ኢሳያስ አሻ፣ ቢሾፕ ጌታሁን ላምቤቦ በአሰልጣኝነት ትምህርት ያቀረቡ ሲሆን የአገልግሎት ኃላፊነትና መሰጠት፣ የማያቋርጥ እድገት፣ ዶክትሪንና አያያዙ፣ የፀሎት ሕይወትና ድምፁን መስማት መለማመድ፣ የአመራርን ፀጋና ጥበብ ማሳደግ፣ በአገልግሎት ጅማሬ ላይ ያሉ ተግዳሮቶችን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ማለፍ፣ የግልና የአካል አገልግሎት፣ የመጨረሻውን ዘመን የቤተክርስቲያን ክብር ማወቅ፣ ዘላለማዊ ዋጋና ክብር ላይ ማተኮር በሚሉ አብይ ርዕሶች ላይ ያተኮሩ ሰፊ የስልጠና ማዕቀፎችን በመዳሰስ አሰልጥነዋል። ስልጠናው የበረከት የመነቃቃትና ራስን በአግባቡ ማየት ያስቻለም እንደነበር ከስልጠናው ተካፋዮች ማረጋገጥ ተችሏል።