በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ውጪ ላላችሁ ቅዱሳን በሙሉ
በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ውጪ ላላችሁ ቅዱሳን በሙሉ እጅግ የምንወዳቸውና የተከበሩ የእግዚአብሔር ሰው አባታችን ቢሾፕ ተክለማሪያም ገዛኸኝ ሰኔ 14 ቀን 2014 ዓ.ም ከዚህ አለም ድካም አርፈው ወደ አምላካቸው መሰብሰባቸው የሚታወቅ ነው:: ከዚህ በፊት በተለያዩ መንገዶች እንደተገለጸው የሽኝት ፕሮግራሙ በአዲስ አበባ ጎፋ ዋናው ጸሎት ቤት የተለያዩ የሃገር ውስጥ እና የውጪ ሃገራት እንግዶች በተገኙበት ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ ይካሄዳል:: …