የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን አመታዊ የአገልጋዮች ሴሚናር
“የምትሄድበት መንገድ ሩቅ ነውና ተነሥተህ ብላ አለው።” 1ኛ ነገሥት 19፥7

የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን አመታዊ የአገልጋዮች ሴሚናር ከህዳር 25-27 ቀን 2016 ዓ.ም በዋራ ቤቴል የኮንፍራንስ ማዕከል ላይ ይካሄዳል። በጉባኤው የሰበካና የቅርንጫፍ ሰበካ ኃላፊዎች፣ የንዑስ ሰበካ ተጠሪዎች፣ የአጥቢያ መጋቢዎችና በተለያየ ደረጃ በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ እያገለገሉ ያሉ የወንጌል አገልጋዮችና ባለቤቶቻቸው ከሃገር ውስጥና ከውጭ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በጉባኤው ለአገልጋዮች መነቃቃትና መታደስ የሚሆኑ ትምህርቶች በኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን መሪዎችና ከውጪ በተጋበዙ አገልጋዮች የሚሰጡ ይሆናል። የፕሮግራሙ አንድ አካል የሆነው ራሳቸውን ለወንጌል ለለዩ አገልጋዮች ደግሞ የስብከትና የክህነት ፈቃድ የመስጠት ስነ-ስርአት እንዲሁ የሚከናወን ይሆናል።

የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን የወንጌል አገልጋይ ነዎት? መልስዎ ‘አዎን” ከሆነ ጊዜዎን አመቻችተው በዚህ  ካህናት ጽድቅና ደህንነት በሚለብሱበት ታላቅ የበረከት፣ የህብረትና የመነቃቃት ጉባኤ ላይ ተገኝተው ከፊትዎ ያለውን የአገልግሎት ሩጫ በድል ሊያስሮጥዎ የሚችልን ስንቅ ይያዙ።

Scroll to Top