33ኛ ው አመት የዋራ-ቤቴል አለማቀፍ ኮንፍራንስ

እንኳን ለ33ኛው አመት የዋራ-ቤቴል አለማቀፍ ኮንፍራንስ በሰላም አደረሳችሁ!

የ33ኛው አመት የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን የዋራ-ቤቴል አለም አቀፍ ኮንፈረንስ በዋራ የኮንፈረንስ ማዕከል ከየካቲት 29- መጋቢት 1 ቀን 2016 ዓ.ም ይካሄዳል።

“መሠዊያ ሥራልኝ፥ የሚቃጠለውንና የደኅንነት መሥዋዕትህን … ሠዋበት፤ ስሜን በማሳስብበት ስፍራ ሁሉ ወደ አንተ መጥቼ እባርክሃለሁ።” [ዘጸአት 20፥24] በሚለው ቃል ኪዳኑ ላለፉት 32 አመታት በዋራ ሜዳ ላይ በታላቅ በረከቱና መጎብኘቱ የባረከን አንዱ አምላክ ኢየሱስ ይባረክ!

በዚህም አመት እግዚአብሔር ቢፈቅድ ብንኖርም ለእግዚአብሔር በተሰበረና በንጹህ ልብ የሚሰዋውን ሰውተን ከመልካሚቱ እጁ ለህይወታችን የሚያስፈልገውን ምህረት፣ ጸጋ፣ በረከት፣ ፈውስና “መንገዱ ይህች ናት!” የሚለውን የቃሉን ምሪትና ምስጢር ለመስማት በጣት የሚቆጠሩ ሳምንታት ቀርተውናል።

ለጉባኤው በቀሩት ቀናት በጥሩ መንፈሳዊ ዝግጅትና ጉባኤውን ከየካቲት 19-21 ቀን 2016 ዓ.ም በታወጀው የጾምና የጸሎት ፕሮግራም እያስረከብን አዳዲስ ነፍሳትን ወደ ጉባኤው በመጋበዝ ጉባኤው የበረከት እንዲሆን ሁላችንም የበኩላችንን እንድንወጣ እንዲሁም ወደ ኮንፈረንሱ የሚደረገው ጉዞ በፍጹም መንፈሳዊ ጨዋነት ይታጀብ ዘንድ በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ቤተክርስቲያን አደራዋን ታሰተላልፋለች።

ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን!

Scroll to Top